Skip to main content
cersa0
በ2018/2025 ግብር ዓመት በየ3 ወሩ የሚከፈለዉ ቅድመ ግብር የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ተደርጓል።
በገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ መሰረት ከተያዘዉ የግብር አመት በፊት በነበረዉ የግብር አመት የተከፈለዉን ግብር 25 በመቶ እንደሚከፈል መደንገጉ ይታወቃል።
በማሻሻያ አዋጁ መሰረት ገቢዎች ሚኒስቴር የ2018/2026 ግብር አመት ዓመታዊ የትርፍ ግብር በየሩብ አመቱ (በየሦስት ወሩ) በማሳወቅ የሚከፈልበት የጊዜ ሰሌዳ አሳውቋል፡፡
በእዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የጊዜ ቀመር ለሚጠቀሙ (ሒሳባቸዉን ሰኔ 30 ለሚዘጉ) ግብር ከፋዮች:-
• የመጀመሪያዉ ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 30 ፣ ከሀምሌ 1- መስከረም 30 የተቀነሰ 3 % ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
• የሁለተኛ ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ ከግንቦት 1 አስከ ግንቦት 30 ፣ከጥቅምት 1 እስከ ታህሳስ 30 የተቀነሰ 3 በመቶ ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል
• የሦስተኛዉ ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ ከነሀሴ 1 እስከ ነሀሴ 30 ፣ከጥር 1 እስከ መጋቢት 30 የተቀነሰ 3 % ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
በ2019 ከሀምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30 አጠቃላይ የ2018 ግብር አመት የትርፍ ግብር ቀድመዉ የከፈሉትን በመቀነስ ቀሪዉን ይከፍላሉ፣ በትርፍ የተከፈለም ካለ ተመላሽ ይጠይቃሉ።
በግሪጎሪያን የጊዜ ቀመር ለሚጠቀሙ (ሒሳባቸዉን ዲሴንበር 30 ለሚዘጉ) ግብር ከፋዮች ፦
• የመጀመሪያዉን ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ August 1 እስከ August 30 ፣ January 1 እስከ March 30 የተቀነሰ 3 % ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
• የሁለተኛ ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ November 1 እስከ November 30 ፣ከApril1 እስከ June 30 የተቀነሰ 3 % ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
በ2026 January 1 እስከ April 30 አጠቃላይ የ2025 ግብር አመት የትርፍ ግብር ቀድመዉ የከፈሉትን በመቀነስ ቀሪዉን ይከፍላሉ፣በትርፍ የተከፈለም ካለ ተመላሽ የሚጠይቁ መሆኑን ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ያወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል ያለው ቲክቫህ ነው።