Skip to main content
cersa5
ዓመታዊ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን በወቅቱ ባላደሱ ነጋዴዎች ላይ ቢሮው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳሰበ!
ታህሳስ፡ 14 ፣ 2018 ዓ/ም ቡታጅራ
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የ2018 አመታዊ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን በወቅቱ ባላደሱ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስቧል፡፡
የቢሮ ምክትል ኃላፊና የንግድ ስርዓትና ሸማች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መላኩ ብርሃኔ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በክልሉ የሚገኙ ነጋዴዎች የበጀት አመቱን የንግድ ስራ ፈቃድ እንዲያድሱ ከሀምሌ 1 ጀምሮ ቅስቀሳ በማድረግ ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ቢሮ ከንግድ ፈቃድ እድሳትና የኦንላይን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያሉ አንዳንድ ችግሮችን ለመፍታት ቀደም ብሎ ለመዋቅሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠቱን ገልጿል።
የበጀት አመቱ ፈቃድ ማደሻ ጊዜ ሊጠናቀቅ 16 ቀናት ብቻ የቀሩት መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ኃላፊው የንግዱ ማህበረሰብ ፈቃዱን አስቀድሞ በማደስ ህጋዊነቱን እንዲያረጋግጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፈቃዳቸውን በወቅቱ ባላደሱ ነጋዴዎች ላይ ቢሮው ከታህሳስ 30 በኋላ በሚያደርገው ክትትል በክልሉ የሚፈጸም ህገ-ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር በወጣው መመሪያ መሰረት እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡
ቢሮው ይህን አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ ለመስጠት በሁሉም መዋቅሮች ባለሙያዎችን መድቦ በየደረጃው ካሉ የንግድ መዋቅር አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት አገልግሎቱን እየሰጡ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው ባሉት ቀሪ ቀናት በኦንላይን ወይም በአካል በመገኝት ተገልጋዮች ፈቃዳቸውን በወቅቱ እንዲያድሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ